📖

ትርጉም በአማርኛ

Meaning in Amharic

ዘመም ይላል እንጂ (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር :: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው ፥ በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤ አዎ ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል :: ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም :: ( አዳምኤል )

✍️

ምሳሌ አጠቃቀም

Example usage in Amharic

የአማርኛ ምሳሌ አጠቃቀም ገና አልተጨመረም።

ይተባበሩን→ contribute
🌿

ባህላዊ ማብራሪያ

Cultural context in Amharic

የባህላዊ ዳራ ማብራሪያ ገና አልተጨመረም።

ይተባበሩን→ contribute
Reference in Englishበእንግሊዝኛ

አስተያየት እና ምላሽ· Likes & comments

No comments yet. Be the first.

ተዛማጅ ይዘቶች · Related posts

See all in ብሎጎች
✍️Bloggeneral

የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል (10,20,…,100)

Read details
✍️Bloggeneral

የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል (10-20)

Read details
✍️Bloggeneral

የግዕዝ ቁጥሮች በአኅዝና በፊደል

Geez numbers

Read details
✍️Bloggeneral

የአቡነ ጴጥሮስ የፅናት ምስክርነት እና የታሪክ አሻራ

Read details